ከጅቡቲ 94 በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎች ወደሀገራቸው ገቡ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ በችግር ውስጥ የነበሩ 94 ኢትዮጵያውያን ወደሀገራቸው መግባታቸው ተገልጿል፡፡
በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት (አይኦኤም) ጋር በመተባበር 94 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ማድረጉን አስታውቋል።
ኤምባሲው ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከሀገር በመውጣት ወደ ሌላው ሀገር መግባት የሰው ልጅ ህይወት ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት እንቀንስ ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡