Fana: At a Speed of Life!

የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን መመስረት የመደመር እሳቤ ውጤት ነው – ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት እና ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተዋህደው የፋና ሚድያ ኮርፖሬሽን አ.ማ መመስረት የመደመር እሳቤ ውጤት ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ገለጹ።

የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የማብሰሪያ እና ሥራ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሐ- ግብሩ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንደገለጹት ፥ በኢትዮጵያ ልክ ኢትዮጵያን መግለጥ ለመቻል በማሰብ ተነጣጥለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ሁለቱ ሚዲያዎች ተዋህደው አንድ ሆነዋል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፣ የሚዲያው አመራሮች የድርጅቱ ሰራተኞች፣ ተባባሪ አዘጋጆች፣ የሚዲያው አጋሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመርሐ- ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።

በዮናስ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.