በጣሊያን በፎረንሲክ ምርመራ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ኦግስቲኖ ፖሌሲ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስና የጣሊያኑ የፖሊስ ተቋም ካራቢነሪ ኮርፕስ በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ሁለቱ ወገኖች በተለይ በፎረንሲክ ምርመራ የልምድ ልውውጥ በማድረግ እና ለፖሊስ አመራሮችና አባላት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በኢትዮጵያ እንዲሁም በጣሊያን ለመስጠት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ከፌዴራለ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ በዚህ ወቅት÷ ጡረታ ለወጡት አቻቸው ለቀድሞው የጣሊያን ካራቢነሪ ኮርፕስ ኮማንደር ጀነራል ቲኦ ሉዙ መልካም ምኞታቸውን ገልፀው፤ አዲስ ለተመደቡት ኮማንደር ጀነራል ሳልቫቶር ሉኦንጎ የእንኳን ደስ አለዎት መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡