Fana: At a Speed of Life!

ወላይታ ሶዶ ከመላው ኢትዮጵያ የተወጣጡ እንግዶቿን እየተቀበለች ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ19ኛዉ የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ለማክበር ከመላው ኢትዮጵያ የተወጣጡ እንግዶች ወደ ወላይታ ሶዶ ከተማ በመግባት ላይ ይገኛሉ።

ከትግራይ፣ ከአማራ፣ ከኦሮሚያ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ከሲዳማ፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያና ከሌሎች አካባቢዎች የተወጣጡ የባህል የልዑካን በድኖች ወደ ወላይታ ሶዶ ከተማ በመግባት ላይ ይገኛሉ ።

የዘንድሮው የብሔር-ብሔረሰቦች በዓል «ሀገራዊ መግባባት ለኅብረብሔራዊ አንድነት» በሚል መሪ ቃል ሕዳር 29 ይከበራል፡፡

በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ አካባቢዎች እየመጡት ላሉት እንግዶች የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል እያደረጉ መሆኑን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.