የጋሞ አደባባይ ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ከ122 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባውን የጋሞ አደባባይ መርቀዋል፡፡
አደባባዩ በዞኑ የሚገኙ ህዝቦችን ባህልና ትውፊት በሚወክል መልኩ መሠራቱም ተጠቁሟል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡