Fana: At a Speed of Life!

የዓለም የንግድ ድርጅት ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ የመጣ ኢኮኖሚ ባለቤት ናት ሲል ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ የመጣ ኢኮኖሚ ባለቤት መሆኗን የዓለም የንግድ ድርጅት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሻንግቼን ዣንግ ገለጹ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሣሁን ጎፌ(ዶ/ር) ከዓለም የንግድ ድርጅት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሻንግቼን ዣንግ ጋር ዛሬ በስውዘርላድ ጄኔቭ ከተማ ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ፥ ኢትዮጵያ በቅርቡ የምታካሂደውን 5ኛውን የዓለም ንግድ ድርጅት የስራ ላይ ቡድን የአባልነት ድርድር ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የዓለም የንግድ ድርጅት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሻንግቼን ዣንግ በዚህ ወቅት ፥ ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ የመጣ ኢኮኖሚ ባለቤት መሆኗን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባል መሆን ለተቀረው ዓለም ተጨማሪ የገበያ ዕድሎችን የሚፈጥር ስለመሆኑ ተነስቷል፡፡

ለዚህም የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ማረጋገጣቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.