በጋምቤላ ክልል 2ኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት መሰጠት ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋምቤላ ክልል ሁለተኛ ዙር የፖሊዮ (የልጅነት ልምሻ) ክትባት ዘመቻ የማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ተካሄደ፡፡
ክትባቱ ስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎችን ጨምሮ በሁሉም ወረዳዎች እና ከተሞቸ 160 ሺህ ለሚጠጉ ሕጻናት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡
ወላጆችና አሳዳጊዎችም ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት አራት ቀናት ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናትን እንዲያስከትቡ ጥሪ መቅረቡን የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
የዓለም ፖሊዮ ቀን “በኢትዮጵያ ፖሊዮን ዜሮ የማድረግ ጉዞ “በሚል መሪ ሐሳብ በጋምቤላ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።