ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለማስቀረት ትውልዱ ላይ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለማስቀረት ትውልዱ ላይ ቀድሞ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
21ኛው የፀረ ሙስና ቀን”ስነ ምግባራዊ ትውልድ ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ሀሳብ በፓናል ውይይት በአዲስ አበባ ከተማ እየተከበረ ይገኛል ፡፡
በውይይቱ ሙስና እና ብልሹ አሰራርንን ለማስቀረት እና የፀረ ሙስና ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ ትውልዱ ላይ ቀድሞ መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል።
ከሙስና የፀዳች ኢትዮጵያን እዉን ለማድረግ በሚሰራው ስራ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበትም መልዕክት ተላልፏል፡፡
በፍቅርተ ከበደ