ጉባኤው በጫካ የቀሩ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላት ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመጡ ጥሪ አቀረበ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በጫካ የቀሩ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላት ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመጡ ጥሪ አቀረበ።
በኦሮሚያ ክልል መንግስት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሰላም ስምምነት በመፈጸማቸው የሰራዊቱ አባላት ወደ ካምፕ መግባት መጀመራቸው ይታወቃል።
የኦሮሚያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፤ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሰላም አማራጭን በመቀበሉ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማው ገልጿል።
በጫካ የቀሩ የሰራዊቱ አባላትም ፈጥነው ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመጡም ጥሪውን አስተላልፏል።
ሰላም እንዲሰፍን የሃይማኖት አባቶች ጸሎት እና ምህላን ሲያደርጉ እንደነበር ያስታወሰው መግለጫው፤ በቀጣይነትም ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ጉባኤው የሰላም ግንባታ ላይ አበክሮ እንደሚሰራ አረጋግጧል።