የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዘርፉ እያበረከተ ላለው የላቀ አስተዋፅዖ ሽልማት ተበረከተለት
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ እያበረከተ ላለው የላቀ አስተዋፅዖ ሽልማት ተበረከተለት።
አየር መንገዱ በናይጄሪያ አቡጃ በተካሄደው የቱሪዝምና ትራንስፖርት ኤክስፖ ለናይጄሪያ የቱሪዝም ኢንደስትሪ ዕድገት በአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ እያበረከተ ላለው የላቀ አስተዋፅዖ ነው ሽልማት የተበረከተለት።
በዚህም “አውትስታንዲንግ ኦንቦርዲንግ ኤክስፔሪያንስ አቺቭመንትስ” ሽልማትን መቀበሉን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡
“የቱሪዝም ኤክስፖ የትራንስፖርት ትስስር ለቱሪዝም ዕድገት” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው የዓመቱ የዕውቅና መርሐ-ግብር ላይ ከአየር መንገዱ በተጨማሪ በአፍሪካ ቱሪዝም ዘርፍ ወሳኝ ሚና ያላቸው የተለያዩ ተቋማት ተሳትፈዋል።