Fana: At a Speed of Life!

አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል አከባበር ዝግጅትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር 19ኛው የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን ለማክበር በአርባምንጭ ከተማ እየተደረገ የሚገኘውን የመጨረሻ ምዕራፍ ዝግጅት ተመልክተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም በዓሉን አስመልክቶ ሲምፖዚየም የሚካሄድበትን አዳራሻ፣ የእራት ምሽት የሚከናወንበትን ስፍራ እንዲሁም የባህል ቡድኖች ትርዒታቸውን የሚያቀርቡበትን የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አባያ ግቢ ስታዲየምን ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ ከአቶ አገኘሁ ተሻገር በተጨማሪ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ፣ የብሄረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አዳማ ትምጳዬ እንዲሁም የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.