Fana: At a Speed of Life!

የብሪክስ ፊልም ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፍሪካ የመጀመሪያው የብሪክስ ፊልም ፌስቲቫል ማስጀመሪያ የሆነው የኢትዮ-ቻይና የፊልምና ቴሌቪዥን ፌስቲቫል በመጪው ወር በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ጎፍ ኢንተርቴይመንት ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እንዲሁም በአዲስ አበባ የቻይና ኤምባሲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ፌስቲቫሉ÷ ከታኅሣስ 11 እስከ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ በሚካሄደው በዚሁ ፌስቲቫል በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ፊልም የሆነው ‘ሂሩት አባቷ ማነው’ እንዲሁም ሌሎች የኢትዮጵያና የቻይና ፊልሞች ለዕይታ እንደሚበቁ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያና ቻይና ፊልሞች በስፋት በሚቀርቡበት በዚሁ መድረክ የብሪክስ ፊልም ፌስቲቫል ይተዋወቃል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

ፌስቲቫሉ የፊልም ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ፣ በኢትዮጵያና ቻይና መካከል ያለውን የልማት ትብብር በሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ለማጠናከር የሚያግዝ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ ነፊሳ አልማህዲ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ የባህል አማካሪ ጃንግ ያዋይ በበኩላቸው ፌስቲቫሉ በሁለቱ ሀገራት መካከል የባህልና ፈጠራ ትብብርን ያጠናክራል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.