Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ የባህልና ጥበባት ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ‘ጥበብና ባህል ለቀጣናዊ ትብብር’ በሚል መሪ ሀሳብ የምስራቅ አፍሪካ የባህልና ጥበባት ፌስቲቫል ከጥር 15 እስከ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ፌስቲቫሉን አስመልክቶ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች በተገኙበት ምክክር እየተደረገ ይገኛል።

በውይይቱ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማሃዲ÷ ፌስቲቫሉ ለቀጣናው ሀገራት ትስስርና ግንኙነት መጠናከር አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።

ምስራቅ አፍሪካ የቋንቋ፣ የባህል እንዲሁም የብዝሃ ማንነት ምንጭ መሆኑን ጠቅሰው÷ ፌስቲቫሉ ቀጣናዊ አንድነትን ያጠናክራል ብለዋል፡፡

በፌስቲቫሉ ባህላዊ ሙዚቃዎች፣ የባህል ኤግዚቢሽኖች፣ ኮንፈረንሶች፣ ፋሽን ትርኢቶችን ጨምሮ በርካታ ሁነቶች መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል፡፡

እንዲሁም በፌስቲቫሉ ላይ በምስራቅ አፍሪካ ባህል፣ ታሪክ፣ እሴትና ሀብቶች ላይ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላት እንደሚሳተፉበት ተመላክቷል፡፡

በዓለምሰገድ አሳዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.