Fana: At a Speed of Life!

ተቋሙ በአለም ተፎካካሪቱን ለማጠናከር ብቁ ባለሙያዎችን በማፍራት አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ነው-ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በአለም አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪቱን ለማጠናከር ብቁ ባለሙያዎችን በማፍራት አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ሲሉ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

 

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷በአቪዬሽን ማሰልጠኛ ተቋማት በነበራቸው ጉብኝት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የአቪዬሽን ዘርፍ ቀዳሚውን ስፍራ ለመያዝ ያላትን ቁርጠኝነት ማየታቸውን ገልፀዋል፡፡

 

ይህንን ከግብ ለማድረስ የመንግስትም ሆነ የግል ማሰልጠኛ ተቋማት እያበረከቱ ያሉት  አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑንም ጠቁመዋል።

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ቀዳሚነቱን ለማስጠበቅና በአለም አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪቱን ለማጠናከር ብቁ ባለሙያዎችን በማፍራት አይነተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

 

መንግስት እና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለእነዚህ ተቋማት ጠንካራ ድጋፍና ክትትል ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉም ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል፡፡

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.