አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የወይቦ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ግንባታ ሒደትን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በወላይታ ዞን የወይቦ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል።
የወይቦ መስኖ ፕሮጀክት የሚገነባው በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ሲሆን÷ የመስኖ መሰረተ ልማቱ የቦሎሶ ሶሬ እና የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ 4 ቀበሌዎችና በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ 7 ቀበሌዎች ውስጥ የሚገኙ አርሶ አደሮችን በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡
የፕሮጀክቱ ግንባታ ተጀምሮ በካሳ ክፍያ ምክንያት የግድቡ ግንባታ ክፍል የቆመ ሲሆን÷ የካናል ሥራው ግን እየተከናወነ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
ከግድቡ ጋር ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት በማድረግ መፍትሔ አቅጣጫ ያስቀምጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡