Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና ፓኪስታን ሕዝቦች ጥልቅ የባሕልና የመንፈስ ትስስር አላቸው – አምባሳደር ጀማል በከር

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮ-ፓኪስታን የወንድማማችነት በዓል ኢስላም አባድ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተከብሯል፡፡

በመርሐ ግብሩ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወዳጅነትና ወንድማማችነት ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ግለሰቦች እውቅና መሰጠቱ ተመላክቷል፡፡

በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር÷ የሚመለከታቸው አካላት ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እድገት ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

መርሐ ግብሩ በሀገራቱ መካከል ያለውን ዘላቂ ግንኙነት የሚያድስ መሆኑን ጠቁመው÷ ሚዲያዎችና የሲቪል ማህበረሰቦች ይህን ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር ረገድ ያላቸውን ጉልህ ሚና ገልጸዋል።

ሚዲያዎች የኢትዮጵያን እና የፓኪስታንን ቀደምት ታሪኮች፣ ባህሎች እና እሴቶች በማስተዋወቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውንም አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ እና በፓኪስታን ህዝቦች መካከል ጥልቅ የባህል እና የመንፈሳዊ ትስስር መኖሩንም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

እያደገ የመጣውን የሁለትዮሽ ግንኙነት በማንፀባረቅ ፓኪስታን የምታራምደውን “ሉክ ኤንድ ኢንጌጅ አፍሪካ” ፖሊሲ እና ሚሲዮኑ ከሚያራምደው ስትራቴጂካዊ ፖሊሲ ጋር አስተሣስሮ በመስራት የጋራ እድገት ላይ እንደሚደርስ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

ይህም የንግድን፣ ባሕል ልውውጥን፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን እና ትብብርን ለማሳደግ ያለመ ሲሆን÷ ኢትዮጵያ ለፓኪስታን ከአፍሪካ ጋር ለመገናኘት መግቢያ በር ያደርጋታል ማለታቸውንም የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.