የቆሼ ደረቅ ቆሻሻ መጣያ ስፍራን ለማልማት የሚያስችል ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተለምዶ ‘ቆሼ’ ተብሎ የሚታወቀውን የደረቅ ቆሻሻ መጣያ ስፍራ ለማልማት የሚያስችል ውይይት እና የመስክ ጉብኝት ተካሄደ።
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሌሊሴ ነሜ እንደገለጹት፤ የአካባቢ ጥበቃ ስርዓትን ለማጠናከር የቆሻሻ አወጋገድ አስተዳደር ያስፈልጋል።
በአዲስ አበባ ከተማ የደረቅ ቆሻሻ መጣያ በሆነው ቆሼ አካባቢ ማህበረሰብ መር የሆነ ስልት በመከተል ቆሻሻን ወደ ሃብት ለመቀየር እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ይህንንም እውን ለማድረግ በኢትዮጵያ የቻይና እና የፈረንሳይ አምባሳደሮች ጋር ውይይት እና የመስክ ጉብኝት መካሄዱን ጠቁመዋል።