Fana: At a Speed of Life!

19ኛውን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን በማስመልከት ሲምፖዚየም ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 19ኛው ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን በማስመልከት በዛሬው ዕለት በአርባምንጭ ከተማ ሲምፖዚየም ይካሄዳል።

‘ሀገራዊ መግባባት ለኅብረብሔራዊ አንድነት’ በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበረውን የ19 ኛው ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን በድምቀት ለማክበር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዝግጅቱን አጠናቋል።

በዓሉን ለማክበር የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምሕረት፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች አርባምንጭ ገብተዋል።

እንዲሁም የተለያዩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ወደ አርባምንጭ ከተማ በመግባት ላይ ሲሆኑ፤ በየአካባቢው በኢትዮጵያዊ የእንግዳ አቀባበል እሴት መሰረት ደማቅ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ከተማ እየተከበረ የሚገኘው 19ኛው ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል አካል የሆነው ሲምፖዚየም በዛሬው ዕለት በጋሞ ባህልና ምርምር ማዕከል አዳራሽ እንደሚካሄድ ታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.