በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር 5 ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር አምስት ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ።
በሳምንቱ የመክፈቻ ጨዋታ በመርሲሳይድ ደርቢ ሊቨርፑል ከኤቨርተን የሚያደርጉት ጨዋታ ቀን 9 ሰዓት ከ30 ይካሄዳል።
ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሶስት ጨዋታዎች ሲደረጉ አስቶንቪላ ከሳውዝሃምፕተን፣ ክሪስታል ፓላስ ከማንቼስተር ሲቲ እንዲሁም ብረንትፎርድ ከኒውካስትል ዩናይትድ ይጫወታሉ።
ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ደግሞ ማንቼስተር ዩናይትድ ኖቲንግሃም ፎረስትን በኦልድትራፎርድ የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ሊጉን ሊቨርፑል በ35 ነጥብ ሲመራ ቼልሲ እና አርስናል በግብ ክፍያ ተበላልጠው በእኩል 28 ነጥብ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
የኮከብ ጎል አስቆጣሪነቱን ደረጃ ሞሃመድ ሳላህ ከሊቨርፑል በ13 ጎሎች እየመራ ይገኛል።