የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ባለሙያዎች አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ የአውሮፕላን አብራሪዎችን ጨምሮ በተለያዩ የአቪዬሽን የሙያ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 450 ሙያተኞች አስመረቀ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይና የፋይናስ ዘርፍ ኃላፊ አዳሙ ታደለ፣ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ካሴ ይማም፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
ስልጠናውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ሙያተኞች 450 ሲሆኑ፤ 115 የአውሮፕላን አብራሪዎች፣ 123 የበረራ መስተንግዶ፣ 84 የጥገና ዘርፍ እና 128 የኮሜርሻል ዘርፍ ሙያተኞች መሆናቸው ታውቋል።
ሰልጣኞቹም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራትና ከሌሎች የተለያዩ አህጉራት የተውጣጡ መሆናቸው መመላከቱን የዘገበው ኢዜአ ነው።