Fana: At a Speed of Life!

በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ያለውን የኃይል አቅርቦት ለማጠናከር በትብብር መስራት እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ያለውን የኃይል አቅርቦት ለማጠናከር ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በትብብር መስራት ይገባል ሲሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ኮርፖሬሽኑ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በልዩ የኢኮኖሚ ዞን ያለን የኃይል አቅርቦት ለማሟላት የሚያስችል ውይይት አድርጓል።

ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) በውይይቱ ወቅት እንዳሉት፤ ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ የሚገቡ ባለሃብቶች ቀዳሚ ጥያቄ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ነው።

በመሆኑም የሃይል አቅርቦትን አስተማማኝ ለማድረግ ከሁለቱ ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የሃይል አቅርቦት ተግዳሮት ሲያጋጥም ተቋማቱ ፈጣን ምላሽ ሲሰጡ መቆየታቸውን አስታውሰው፤ ይህ ፈጣን ምላሽ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ÷ በኮርፖሬሽኑ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና የሃይል አቅርቦቱን በተሟላ ሁኔታ ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የሚያጋጥሙ ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት የሚያስችል ከሶስቱ ተቋማት የተውጣጣ የጋራ ኮሚቴ መዋቁሩን ጠቁመው፤ ኮሚቴው በጋራ ለመስራትና የሃይል መቆራረጦች ሲጋጥሙ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ ያደርጋል ማለታቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.