የመርሲሳድ ደርቢ በአየር ሁኔታ ምክንያት ተራዘመ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጉዲሰን ፓርክ ሊካሄድ የነበረው የሊቨርፑል እና ኤቨርተን ጨዋታ በአየር ሁኔታ ምክንያት መራዘሙን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አስታወቀ፡፡
የመርሲሳድ ደርቢ ቀን 9 ሰዓት ከ30 ሊደረግ ቀጠሮ ቢያዝለትም የአየር ሁኔታው ጨዋታ ለማካሄድ የማያስችል ከባድ የአየር ሁኔታ በመከሰቱ ምክንያት በዛሬው እለት እንደማይደረግ ተገልጿል።
ጨዋታው የሚደረግበት ቀን እና ሰዓት በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡
በእንግሊዝ መርሲሳድ የተከሰተው ከባድ አውሎ ነፋስ በሰዓት 112 ኪሎ ሜትር ልኬት እንዳለው የተገለፀ ሲሆን ነፋሱ በተጨዋቾች እና ደጋፊዎች ላይ ተፅዕኖ ሊያደርስ የሚችል በመሆኑ ጨዋታው ተራዝሟል።