ከ575 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ575 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግንባታ እቃዎች፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ የተለያዩ ማእድናት፣ ተሽከርካሪዎች እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ ፌደራል ፖሊስ፣ የክልል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት ሲሆን፤ በፍተሻ፣ በደፈጣ እና በበረራ የተያዙ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 17 ተጠርጣሪ ግለሰቦች እና አምስት ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡