ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ በብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ላይ ለመታደም አርባምንጭ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ላይ ለመታደም አርባምንጭ ከተማ ገብተዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ÷ “በልምላሜ ከተሞሸረችው፣ ከውበት ሰገነቷ ስፍራ፣ ከተፈጥሮ የቅኔ መዳረሻ፣ ከሰው አክባሪዎቹና ከሸማ ፈታዮቹ ምድርና ከአርባ ምንጮቹ መገኛ አርባ ምንጭ ከተማ ገብተናል” ብለዋል፡፡
አርባ ምንጭ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱምለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ለአርባ ምንጭ ከተማ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡