ማንቼስተር ሲቲ እና ክሪስታል ፓላስ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ15ኛ ሳምንት የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወደ ሴልሁሩስት ፓርክ ያቀናው ማቼስተር ሲቲ ከክሪስታል ፓላስ ጋር 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡
በጨዋታው ለክሪስታል ፓላስ ግቦቹን ሙኖዝ እና ላክሮይክስ ሲያስቆጥሩ ለማንቼስተር ሲቲ ደግሞ ኤርሊንግ ሃላንድ እና ሪኮ ልዊስ አስቆጥረዋል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት በተደረጉ ጨዋታዎች አስቶንቪላ ሳውዝአምፕተንን 1 ለ 0 እንዲሁም ብሬንትፎርድ ኒውካስል ዩናይትድን 4 ለ 2 አሸንፈዋል፡፡
ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ላይ ማንቼስተር ዩናይትድ ኖቲንግሃም ፎረስትን በኦልድትራፎርድ ያስተናግዳል፡፡