ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) የአርባምንጭ ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት የደረሰበትን ደረጃ ገመገሙ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአርባ ምንጭ ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት የደረሰበትን የእድገት ደረጃ ገምግመዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷”ከአምስት ወራት በፊት ከነበረኝ ጉብኝት በመቀጠል ዛሬ የአርባምንጭ ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት የደረሰበትን የእድገት ደረጃ ገምግመናል “ብለዋል፡፡
ይህ ሥራ የሀገራችንን የቱሪዝም አቅም የሚያጠናክር የአካባቢውን አስደናቂ የተፈጥሮ መልክዓ ምድር እና የተትረፈረፈ ሀብት ቆጥሮ የሚጠቀም ሁሉን ያካተተ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ቱሪዝምን ከማሳደግ ባሻገር ለአካባቢው ማኅበረሰብ ፕሮጀክቱ ትርጉም ባለው ደራጃ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል፡፡
እነዚህን መሰል ሥራዎች በስኬት ሥራ ሲጀምሩ ለዘላቂ ልማት እና ብልፅግና መንገድ የሚጠርጉ እንደሚሆኑም አመልክተዋል፡፡