Fana: At a Speed of Life!

ዴንማርክ የኢትዮጵያን የሪፎርም ስራዎች እንደምትደግፍ ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዴንማርክ የኢትዮጵያን የሪፎርም ስራዎች ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን ገልፃለች፡፡

 

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ከዴንማርክ የገንዘብ ሚኒስትር  ኒኮላይ ዋመን ጋር ተወያይተዋል፡፡

 

በውይይቱ አቶ አህመድ ሺዴ÷ የዴንማርክ መንግስት ለኢትዮጵያ በግብርና፣ በምግብ ዋስትና፣ በኑሮ መሻሻል እና አስተዳደር ዘርፎች ለሚያደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

 

ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ከዴንማርክ ጋር  በታዳሽ ሃይል፣በዘላቂ የግብርና ልማት እና በአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ትብብሯን ማጠናከር እንደምትፈልግ ገልጸዋል፡፡

 

እንዲሁም ኢትዮጵያ ያካሄደችውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የውጭ እዳ ቅነሳ ስራዎችን በማብራራት  የዴንማርክ መንግስት ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

 

ኒኮላይ ዋመን በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ያካሄደቻቸው ሪፎርሞች እና በሁሉም ዘርፎች ያሳየችው እምርታ እውቅና የሚሰጠው ነው ብለዋል፡፡

 

የዴንማርክ መንግስት የኢትዮጵያን የሪፎርም ስራዎች ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑንም መግለፃቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.