Fana: At a Speed of Life!

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በአርባ ምንጭ ከተማ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት እየተከበረ ነው።

በአከባበር ሥነ-ሥርዓቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የሕዝብ ተወካዮቸ ም/ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ እና የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ተገኝተዋል፡፡

እንዲሁም የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች፣ የብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በበዓሉ ታድመዋል፡፡

በዓሉ “ሀገራዊ መግባባት ለሕብረብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡

ባለፉት ቀናት ሲከበር በቆየው 19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ ሁነቶች ተከናውነዋል፡፡

ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ልምዳቸውን፣ ተሞክሯቸውን፣ ባሕላቸውን፣ እሴቶቻቸውን የተለዋወጡባቸው መርሐ ግብሮች መዘጋጀታቸውም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.