Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ ለውጡ ከይስሙላ ፌዴራሊዝም ወደ ዕውነተኛ ፌዴራሊዝም ያሸጋገረ ነው – አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገራዊ ለውጡ ከይስሙላ ፌዴራሊዝም ወደ ዕውነተኛ ፌዴራሊዝም ያሸጋገረ ነው ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡

19ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአርባ ምንጭ ከተማ በታላቅ ድምቀት ተከበረ ።

አቶ ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት÷ የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል በአርባ ምንጭ ከተማ የሩቅና የቅርብ ጠላቶችን ተስፋ በሚያስቆረጥ መልኩ በድምቀት መከበሩን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ውበትና ፀጋ የሚታደሉት እንጂ የሚታገሉት እንዳልሆነም አውስተዋል፡፡

ብልፅግና ፈተናዎችን አልፎ ተስፋ ያላትና አስተማማኝ ሀገር እንድትሆን አስችሏል ነው ያሉት።

ሀገራዊ ለውጡ ከይስሙላ ፌዴራሊዝም ወደ ዕውነተኛ ፌዴራሊዝም ያሸጋገረ እንዲሁም ነጠላ ትርክትን ወደ ብሔራዊ ትርክት በመቀየር ቱርፋት ነበረው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ወደ ብልፅግና ያሻገሩ ፈተናዎችን ወደ ኃይል ለለወጡት፣ የሀሳብ አፍላቂና የለውጡ ፋና ወጊ ለሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምስጋና ማቅረባቸውን ከክልሉ ኮሙኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.