Fana: At a Speed of Life!

ነጻነታችን የሚጋፋ ማንኛውንም የውጭ ሃይል በጋራ በማንበርከክ አንድነታችንን ጠብቀን ኖረናል – ፕሬዚዳንት ታዬ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያውያን ሰላምና ነጻነታችን የሚጋፋ ማንኛውንም የውጭ ሃይል በጋራ በማንበርከክ አንድነታችን ጠብቀን ኖረናል ሲሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንት ታዬ 19ኛውን የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም ኢትዮጵያውያን ሰላምና ነጻነታችን የሚጋፋ ማንኛውንም የውጭ ሃይል በጋራ በማንበርከክ አንድነታችን ጠብቀን ኖረናል ብለዋል።

ኅብረ ብሔራዊ፣ ለሀገሩ ቀናዒ የሆነና ልማትን ዕውን ለማድረግ የወሰነ ትውልድ ሰላሙንም በአስተማማኝነት ያጸናል ነው ያሉት፡፡

ካለመግባባት የምናተርፈው፣ ከልማት የምናጣው፣ ከሰላም የምናጎድለው እንደሌለ ከእኛ የተሻለ የተገነዘበ ሊኖር አይችልም ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ስለሆነም ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን በዕኩልነትና በፍትህ መሠረቶች ላይ ይበልጥ በማጽናት ጠንካራ፣ የበለፀገች፣ የታፈረችና የተከበረች ኢትዮጵያን እንገንባ ብለዋል ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.