Fana: At a Speed of Life!

በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ አበረታች ውጤት መመዝገቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ላይ አበረታች ውጤቶችን አስመዝግባለች ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴዔታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

በአልጄሪያ እየተካሄደ ባለው 3ኛው የፓን አፍሪካ ስታርታፕ ኮንፈረንስ ላይ በሚኒስትር ዴዔታው የተመራ ልዑክ እየተሳተፈ ነው፡፡

በዚሁ ወቅትም ኢትዮጵያ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አበረታች ውጤቶች ማስመዝገቧን ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ለአብነትም በኢንተርኔት አገልግሎት፣ በሞባይል ገንዘብ አገልግሎት፣ በብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ እና የቴሌኮም ዘርፍ ለገበያ ነፃ በማድረግ ኢትዮጵያ በዘርፉ እያስመዘገበች ያለውን ዕድገት አብራርተዋል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውሎት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትንም አንስተው÷ ዘርፉ በግብርና፣ ጤና፣ ትምህርትና አሥተዳደር ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ቁልፍ መሣሪያ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በኮንፈረንሱ ከአፍሪካ የተወጣጡ ከ25 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች፣ ከ300 በላይ ባለሃብቶችና ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተሰባሰቡ ስታርታፖችን እየተሳተፉ መሆኑን በአልጀሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.