ለካሳንችስ ልማት ተነሺዎች በገላን ጉራ የተገነባዉና ዛሬ አገልግሎት የሚጀምረው የገላን ጉራ የመኖሪያ እና የተቀናጀ የልማት መንደር በውስጡ ምን ይዟል?
በ1 ሺህ 200 መኖሪያ ቤቶች 6500 ነዎሪዎችን የያዘ መኖሪያ መንደር ነው።
- 1.6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለዉ የአስፋልት መንገድ አለው።
- ከ20 በላይ አውቶቡሶችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚያስችል ተርሚናል አለው።
- በ2 ወር ጊዜ ዉስጥ የተገነቡ ከቅድም አንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ያሉ ትምህርት ቤቶች ከነምገባ ማዕከሉ ይዟል።
- በ3 ሺፍት ለ270 እናቶች የስራ እድል የፈጠረ የእንጀራ መጋገርያ ፋብሪካ አለው።
- 500 አረጋዉያን እና አቅመ ደካሞችን በቀን አንድ ጊዜ መመገብ የሚያስችል የምገባ ማዕከል አለው።
- በቀን 60 ሺህ ዳቦ የማምረት አቅም ያለው የዳቦ ፋብሪካ እና የዕህል ወፍጮዎችን ይዟል።
- ደረጃውን የጠበቀ የህጻናት መጫወቻ እና የህጻናት ማቆያ አለው።
- ሁለት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲሁም አረንጓዴ ቦታዎችና መናፈሻዎች ተገንብተዋል።
- በቋሚ እና በጊዜያዊነት ለ1 ሺህ 646 ነዋሪዎች የስራ እድል መፍጠር መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መረጃ አመልክተዋል።