Fana: At a Speed of Life!

በብሬል የተዘጋጀው የግዢና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ይፋ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴራል የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1333/2016 በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋ በብሬል ተዘጋጅቶ ለዓይነሥውራን ዜጎች ለአገልግሎት ቀረበ፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ በዚህ ወቅት÷ አዋጁ በብሬል እንዲዘጋጅ የተደረገው ዓይነሥውራን ዜጎች ስለአዋጁ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና አዋጆችና ደንቦች ሲዘጋጁ አካል ጉዳተኞችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያካተቱ እንዲሆኑ ታሳቢ በማድረግ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን አዋጁን በብሬል አዘጋጅቶ ለዓይነሥውራን ዜጎች ማቅረቡ አርአያነት ያለው ተግባር መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ሌሎች የመንግስት ተቋማትም አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ ሲያዘጋጁ አካል ጉዳተኛ ዜጎችን ታሳቢ እንዲያደርጉ አቶ አህመድ ሺዴ ማሳሰባቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

በብሬል የተዘጋጀው የፌዴራል የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር አዋጅ በኢትዮጵያ ዓይነሥውራን ብሄራዊ ማህበር፣ በአብርሆት ቤተመጻህፍት፣ በገንዘብ ሚኒስቴር ቤተመጻፍትና በሌሎች ለአገልግሎት ምቹ በሆኑ ስፍራዎች እንደሚቀመጥ ታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.