Fana: At a Speed of Life!

ሐሰተኛ የደረሰኝ ህትመትን ለመከላከል ያለመ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ገቢዎች ሚኒስቴር እና ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በደረሠኞች ላይ ልዩ መለያ ኮድ (QR-Code) አካቶ ማተም በሚያስችል አሠራር ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ ከታክስ ደረሰኝ ህትመት ጋር በተያያዘ ልዩ መለያ ኮድ ተካቶ ማተም፣ የህትመት ጥያቄ መቀበል፣ ከታተመ በኋላ የስርጭት እና የቁጥጥር ሥርዓትን ማስፈን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት የሚያስችል ነው፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ የሐሰተኛ ደረሰኝ ህትመት በግብር አሰባበሰቡ ላይ ፈተና ሆኖ መቆየቱን ገልጸው÷ ይህን ችግር ለመፍታት ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ጋር በጋራ ለመሥራት ስምምነቱ መፈረሙን አስረድተዋል፡፡

የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሽታሁን ዋለ ድርጅታቸው ሚስጥራዊ ህትመቶችን በማተም የካበት ልምድ እንዳለው ጠቅሰው÷ ደረጃውን የጠበቀ፣ ልዩ መለያ ኮድ (unique QR code) የተካተተበት እና አስመስሎ መስራት በማይቻል መልኩ የህትመት ሥራውን ለማከናወን ዝግጅት ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

ግብር ከፋዮች ለገቢዎች ሚኒስቴር በሚያቀርቡት የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ መሠረት የሚቀርቡ የህትምት ትዕዛዞችን ተቀብሎ ደረሰኞችን ለማተም በቂ ዝግጅት ማድረጉንም አንስተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.