Fana: At a Speed of Life!

የቼክ ሪፐብሊክ ልዑክ በኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቼክ ሪፐብሊክ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት የተመራ የቢዝነስ ልዑካን ቡድን አባላት የቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን ጎበኙ፡፡

ልዑኩ በመኪና መገጣጠም፣ በሕክምና ቁሳቁስ ምርት፣ በንግድና ሌሎችም ተያያዥ ዘርፎች ላይ ለመሰማራት የሚፈልጉ ባለሀብቶችና የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዘመን ጁነዲ÷ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ስለሚሰጡ ማበረታቻዎች፣ የኢንቨስትመንት ዘርፎች፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ይበልጥ ለመሳብ በተደረጉ የኢኮኖሚ ሪፎርም ማሻሻያ ተግባራት ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

በኢኮኖሚ ሪፎርም ማሻሻያው ምክንያት አሁን ላይ ከፍተኛ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍላጎት ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች እየታየ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

የልዑኩ አባላት በበኩላቸው የኢኮኖሚ ዞኖቹ ዘመናዊ ከመሆናቸው በተጨማሪ ባደጉት ሀገራት ካሉ የኢኮኖሚ ማዕከላት ጋር የሚወዳደሩ መሆናቸውን አይተናል ማለታቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.