Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና አልጄሪያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 3ኛው የአፍሪካ ስታርት አፕ ጉባዔ እና አውደ-ርዕይ በአልጄሪያ አልጀርስ እየተካሄደ ነው።

ከጉባዔው ጎን ለጎን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴዔታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) ከአልጄሪያ የዕውቀት ኢኮኖሚ፣ ስታርት አፕና ማይክሮ ኢንተርፕራይዝ ሚኒስትር ኑረዲን ኡዳህ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ሁለቱ ተቋማት በኢኖቬሽን፣ በቴክኖሎጂ፣ በምርምርና በሰው ሃይል አቅም ግንባታ ላይ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

ባይሳ በዳዳ(ዶ/ር) ÷ኢትዮጵያ የስታርት አፕ ሥነ-ምህዳር ላይ ሰፋፊ ሥራዎችን በመስራት ዜጎች ከዘርፉ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሥርዓት ግንባታ ላይ እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል።

ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች፣ ባለሃብቶችና ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በዘርፉ በትብብርና በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ መግለጻቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.