የአለም ንግድ ድርጅት ድርድር ብሔራዊ ኮሚቴ አባላት በ5ኛዉ የሥራ ቡድን ስብሰባ ሠነዶች ላይ ምክክር እያካሄዱ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ የአለም ንግድ ድርጅት ድርድር ብሄራዊ ኮሚቴ አባላት ኢትዮጵያ በቅርቡ በምታካሂደው 5ኛው የስራ ቡድን ስብሰባ ስነዶች ላይ በጄኔቫ የአለም ንግድ ድርጅት ዋና ፅህፈት ቤት እየተወያዩ ነው፡፡
በምክክሩ በዝርዝር የድርድር ነጥቦች ዙሪያ የተግባር ልምድና የተሞክሮ ልውውጥ እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያ የአለም ንግድ አባልነትን በመቀላቀል ምርቶቿንና አገልግሎቶቿን በጥራትና በተወዳዳሪ ዋጋ ለዓለም ገበያ በማቅረብ የውጪ ምንዛሪ ገቢዋን ለማሳደግ ተኪ የሀገር ውስጥ ብዝሃ ምርቶችን መጠንና ጥራት ከማሳደግ በተጓዳኝ የንግድ ሥርዓቱን እያዘመነች ትገኛለች።