Fana: At a Speed of Life!

ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ ከቼክ ሪፐብሊክ አቻቸው ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያን ዩሬችካ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙርያ ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ በርካታ ዓመታትን የዘለቀውን የኢትዮ-ቼክ ግንኙነት ለማጠናከር በረጅም ጊዜ የብድር ስምምነት እና በልማት ትብብር ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመናል ብለዋል፡፡

የቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለችውን የልማት እንቅስቃሴ ማድነቃቸውን ጠቅሰው፤ በተለይም የቼክ መንግሥት በቱሪዝም እና በዱር እንስሳት ጥበቃ ዙርያ በትብብር ለመሥራት ፍላጎት እንዳለው ገልጸውልኛል ብለዋል፡፡

በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ የሀገራቱ ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከስምምነት ላይ ደርሰናልም ነው ያሉት፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.