Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያና ቼክ ሪፐብሊክ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰራ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያን ዩሬችካ ጋር ተወያይተዋል።

ጌዲዮን (ዶ/ር) የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በኢኮኖሚ፣ በኢንዱስትሪ፣ በንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ለማጠናከር መሥራት እንደሚገባ አንስተዋል።

የሀገራቱ ግንኙነት ዘመናትን ያስቆጠረና ትርጉም ባለው አጋርነት የተጋመደ መሆኑን በማንሳት በኢትዮጵያ በርካታ ኢንዱስትሪዎች በቼክ ሪፐብሊክ የቴክኒክ እና የፋይናንስ ድጋፍ መገንባታቸውን እንደ ማሳያ ገልጸዋል።

ቼክ ሪፐብሊክ የአውሮፓ ሕብረት አባልነቷንና በሕብረቱ ውስጥም የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገር መሆኗን ጠቁመው÷ ወዳጅነቱን የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።

ማሪያን ጁሬስካ በበኩላቸው ÷በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከተለያዩ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

የቢዝነስ ልዑካን መርተው መምጣታቸውን በመግለጽ÷ በቆይታቸው የኢትዮ-ቼክ ሪፐብሊክን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት የሚያጠናክር ሥራ መሠራቱን ተናግረዋል።

ማሪያን ጁሬስካ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቁልፍ አጋር በመሆኗ ለግንኙነቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጡ መጥቀሳቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.