ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ከአውሮፓ ህብረት ልዑካን ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በአውሮፓ ህብረት የልማት ጉዳዮች ዋና አስተባባሪ ሮቤርቶ ሽሊሮ ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በተለያዩ ዘርፎች በሶማሌ ክልልና በአውሮፓ ህብረት መካከል በሚኖረው ትብብር ዙሪያ መክረዋል፡፡
የክልሉ መንግስት በሚያከናውናቸው የልማት ሥራዎች ላይ ህብረቱ ድጋፍ በሚያደርግባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት መደረጉንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡