Fana: At a Speed of Life!

የክልላዊ የአጀንዳ ልየታ ምክክር መድረክ አመቻቾች ስልጠና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተመረጡ የኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ልየታ የምክክር መድረክ 48 አመቻቾች ስልጠና በአዳማ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ክልላዊ የአጀንዳ ልየታ የምክክር መድረክ ታሕሣሥ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

የክልላዊ ምክክሩ ዋና አስተባባሪ ብዙነህ አሰፋ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ÷ አመቻቾቹ እውቀት ላይ ተመስርተው እንዲሰሩ፣ አጀንዳዎችን መሰብሰብ እንዲችሉ፣ ከተወያይ የህብረተሰብ ወኪሎች መካከል ለሀገራዊ ምክክሩ ተወካዮችን መምረጥና ምክክሩን ከተለያዩ ተፅዕኖዎች እንዲከላከሉ የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

አመቻቾቹ ከዚህ በፊት በህብረተሰብ ወኪሎች መረጣ ወቅት ከኮሚሽኑ ጋር የሰሩና ተከታታይ ስልጠናዎችን ሲወስዱ የቆዩ መሆናቸውንም አስታውሰዋል፡፡

እንዲሁም ዛሬን ጨምሮ ለሥድስት ቀናት ከኮሚሽኑ ጋር ከምክክሩ ጋር የተያያዙ ስልጠናዎችንእንደሚወስዱ እና የልምድ ልውውጦችን እንደሚያደርጉ አመላክተዋል፡፡

በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.