Fana: At a Speed of Life!

በገላን ጉራ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በትናንትናው ዕለት የተመረቁትና በገላን ጉራ የሚገኙት ሦስት ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ ጀምረዋል፡፡

የመማር ማስተማር ስራውን ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር) ናቸው፡፡

የቢሮ ሃላፊው ለተማሪዎች እንኳን ደስአላችሁ ያሉ ሲሆን ፥ ተማሪዎች ለመማር ማስተማር ስራው ምቹ ሆነው በተገነቡት ትምህርት ቤቶች እየተማሩ የላቀ ውጤት ለማምጣት እንዲተጉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመማር ማስተማር ማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊዎችና ሌሎች አመራሮች መገኘታቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.