Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካን የኢንዱስትሪ ዕድገት ለማፋጠን ለወጣትና ሴት ሥራ ፈጣሪዎች የሚደረገው ድጋፍ ይጠናከራል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ሳምንት የሴቶችን አቅም ማጎልበት፣ የአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጣና ዕድሎችን መጠቀም፣ አጋርነትን ማጠናከር እና ፈጠራን ማበረታታት ታሳቢ በማድረግ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ የስራ ፈጠራና ቱሪዝም ዲቪዥን ሃላፊ ሮን ኦስማን ኦማር በዚህ ወቅት፥ እያደገ የመጣው የቴክኖሎጂ ፈጠራ የአህጉሪቱን ግቦች ለማሳካት አጋዥ ነው ብለዋል።

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን፣ ከብክለት የጸዳ ኢንዱስትሪንና ቴክኖሎጂን በማስፋፋት አጀንዳ 2063ን ማሳካት እንደሚቻል ጠቁመዋል።

የሥራ ፈጠራ አቅም ያላቸው አፍሪካውያን ሴቶች በኢንዱስትሪ ጉዞ የሚያጋጥማቸውን ችግር እንዲፈቱ የህብረቱ ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት በአህጉሩ የኢንተርፕራይዝ ማዕቀፍ መሰረት ወጣትና ሴት የስራ ፈጣሪዎችን እየደገፈ እንደሚገኝ ገልጸው፥ በዚህም በርካታ ወጣቶች የፈጠራ ምርቶቻቸውን ኤክስፖርት ማድረግ ጀምረዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በቀጣይም የአህጉሪቱን የኢንዱስትሪ ዕድገት ለማፋጠንና የህብረቱን የ2063 ግቦችን ለማሳካት ለወጣትና ሴት ስራ ፈጣሪዎች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

በኢንዱስትሪ ሳምንቱ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ሴቶች የፈጠራ ስራዎቻቸውን ለዕይታ ማቅረባቸውንም ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.