Fana: At a Speed of Life!

የጅግጅጋን የኮሪደር ልማት በ3 ወራት ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ እየተገነባ ያለውን የጅግጅጋ ከተማ ኮሪደር ልማት ሥራ በሦስት ወራት በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ለማብቃት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የኮሪደር ልማቱ በከተማዋ ሁለት አቅጣጫዎች እየተካሄደ መሆኑን የገለጹት የጅግጅጋ ከተማ ከንቲባ ሻፊ አሕመድ (ኢ/ር)÷ በኮሪደር ልማቱ 30 ኪሎ ሜትር መንገድ እንደሚለማ ጠቁመዋል፡፡

የመንገድ መሠረተ-ልማት፣ ኤሌክትሪክ፣ የቴሌኮም መስመሮች፣ የፍሳሽ ማስወገጃ፣ የቤቶች ግንባታና እድሳት፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ የመኪና ማቆሚያ፣ አረንጓዴ ልማትና ሌሎች ሥራዎችን መካተታቸውንም አብራርተዋል፡፡

የኮሪደር ልማቱ ሲጠናቀቅም የከተማዋን ገፅታ በማሳደግ የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እና የከተማዋን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማፋጠን ያስችላል ማለታቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.