Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የጥራት መንደርን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተለያዩ የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት በአንድ ላይ የሚገኙበትን የጥራት መንደር ጎብኝተዋል።

ፕሬዚዳንት ታዬ በጥራት መንደሩ የሚገኙ ተቋማት በጤና ዘርፍ፣ በኮንስትራክሽን፣ በግብርና ውጤቶች፣ በምግብና መጠጥ ዘርፎች እና በኢንዱስትሪ ግብዓቶችና በተለያዮ ዘርፎች ገቢና ወጪ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ጥራት የሚያረጋግጡ የላቦራቶሪ መሳሪያዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የጥራት መሠረተ ልማት ተቋማት አመራሮች ለፕሬዚዳንቱ ስለ ጥራት መንደሩ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን፤ የጥራት መንደሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት እንደተጀመረ አስታውሰዋል።

መንደሩ ግንባታ 8 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገበትና ጥራትን የሚያረጋግጡ ዘመናዊ የላቦራቶሪና የቢሮ ግንባታ የያዘ መሆኑን መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

ሌላኛው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አብዱልሃኪም ሙሉ (ዶ/ር) በበኩላቸው የጥራት መንደሩ የገቢና ወጪ ምርቶችን ጥራት በማረጋገጥ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.