Fana: At a Speed of Life!

በመታጠቢያ ቤት ወድቀው ጉዳት የደረሰባቸው የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ከህመማቸው ማገገማቸው ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ በአንጎል ውስጥ የደም መፍሰስ ምክንያት ቀዶ ጥገና ከተደረገላቸው በኋላ በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡

የ79 ዓመቱ ዳሲልቫ በዋና ከተማዋ ብራዚሊያ ውስጥ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በመታጠቢያ ቤት ወድቀው ጉዳት ከደረሰባቸው በኋላ ከባድ የራስ ምታት እንደተሰማቸው የተገለጸ ሲሆን ፥ በትናትናው ዕለት ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተገልጿል።

በዚህም የኤም አር አይ እና ሌሎች ምርመራዎች ከተደረገላቸው በኋላ ሳኦ ፖሎ ወደሚገኘው ታዋቂው የሲሪዮ-ሊባንዬስ ሆስፒታል መዛወራቸውም ነው የተነገረው።

ሆስፒታሉ በሰጠው መግለጫም ፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ በቅርቡ በመኖሪያቸው በሚገኘው መታጠቢያ በመውደቃቸው ምክንያት የውስጥ ጭንቀላት ደም መፍሰስ ችግር እንዳጋጠማቸው ገልጿል፡፡

ሀኪሞቻቸው÷ ፕሬዚዳንቱ ከቀዶ ጥገናው በኋላ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙና ጤንነታቸው መሻሻሉን በዚሁ ከቀጠለም በቀጣይ ሣምንት ከሆስፒታል ይወጣሉ ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.