አቶ ሽመልስ አብዲሳ በምስራቅ ባሌ ዞን የግብርና ልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በምስራቅ ባሌ ዞን እየተከናወኑ ያሉትን የግብርና ልማት ስራዎችን ጎብኝቷል፡፡
ልዑኩ በምስራቅ ባሌ ዞን በመገኘት በኩታ ገጠም እርሻ የለሙ የዘንጋዳ እና የጤፍ ሰብሎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል።
በዞኑ በ2016/17 የመኸር ወቅት 508 ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች መሸፈኑ ተገልጿል።
በምስራቅ ባሌ ዞን የሚገኙ አርብቶ አደሮች የግብርና ስራ ላይ በመሰማራት የዝናብ ወቅት እና መስኖን በመጠቀም የተለያዩ የሰብል አይነቶችን እያመረቱ እንደሚገኙ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ልዑኩ ከግብርና ልማት ስራዎች በተጨማሪ በዞኑ የተከናወኑና እየተከናወኑ ያሉ ሌሎች የልማት ስራዎችንም እንደሚጎበኝ ታውቋል።