Fana: At a Speed of Life!

የኬንያ መከላከያ ኮሌጅ ልዑክ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኬንያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ የሥራ ሃላፊዎችና የኮሌጁ ሰልጣኞች ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎብኝተዋል፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሀሰን÷ የአየር መንገዱን የተለያዩ አገልግሎቶችና መሠረተ ልማቶችን አስጎብኝተዋል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት በጉብኝታቸው የአየር መንገዱን የካርጎ ተርሚናል፣ የበረራ መማሪያ ሲሙሌተር፣ የአየር ትራፊክ ቁጥጥር ስራንና ሌሎችንም አገልግሎቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በዚሁ ወቅት አቶ በርኦ ሀሰን÷ የአየር መንገዱን መሠረተ ልማት በማስፋፋትና የዘርፉን ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ በማዋል አገልግሎቶችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በተሰራው ስራ ውጤታማ ሆነናል ብለዋል።

አየር መንገዱ አፍሪካን ለማስተሳሰርና ከዓለም ጋር ለማገናኘት እየሰራ ነውም ማለታቸውን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የልካን ቡድኑ አባላት በነበራቸው ጉብኝት ጠቃሚ ተሞክሮ ማግኘታቸውን ገልፀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.