Fana: At a Speed of Life!

የመንገድ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ትኩረት እንዲሰጥ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገራዊ የመንገድ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ ማጠናቀቅ እንዲቻል በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡

ለፕሮጀክቶቹ የሚመደበውን በጀት ተግባራዊ ለማድረግ በየደረጃው ያሉ የመንግስት መዋቅሮችን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን መወጣት በሚችሉበት አግባብ ላይ ውይይት መካሄዱን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስትር ዴዔታ የትምጌታ አስራት፥ የጸጥታ ችግሮች፣ የካሳ ክፍያ፣ የሲሚንቶ፣ ነዳጅ የመሳሰሉት ግብዓቶች በሚፈለገው ሁኔታ አለመገኘት ፕሮጀክቶችን ከመጓተት እስከመቋረጥ የሚያደርሱ ማነቆዎች መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

ተግዳሮቶቹ በወቅቱ እንዲፈቱ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲፈታ ሚኒስቴሩ ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል፡፡

ከገንዘብ ሚኒስቴር የተሳተፉ ባለሙያዎች የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እስከተወጣ ድረስ ተግዳሮቶችን ለከፍተኛ አመራሩ በማቅረብ እንዲፈቱ ማድረግ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡የመንገድ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ትኩረት እንዲሰጥ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገራዊ የመንገድ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ ማጠናቀቅ እንዲቻል በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡

ለፕሮጀክቶቹ የሚመደበውን በጀት ተግባራዊ ለማድረግ በየደረጃው ያሉ የመንግስት መዋቅሮችን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን መወጣት በሚችሉበት አግባብ ላይ ውይይት መካሄዱን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስትር ዴዔታ የትምጌታ አስራት፥ የጸጥታ ችግሮች፣ የካሳ ክፍያ፣ የሲሚንቶ፣ ነዳጅ የመሳሰሉት ግብዓቶች በሚፈለገው ሁኔታ አለመገኘት ፕሮጀክቶችን ከመጓተት እስከመቋረጥ የሚያደርሱ ማነቆዎች መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

ተግዳሮቶቹ በወቅቱ እንዲፈቱ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲፈታ ሚኒስቴሩ ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል፡፡

ከገንዘብ ሚኒስቴር የተሳተፉ ባለሙያዎች የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እስከተወጣ ድረስ ተግዳሮቶችን ለከፍተኛ አመራሩ በማቅረብ እንዲፈቱ ማድረግ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.