Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ለአሜሪካ ከላከቻቸው መኪኖች ሽያጭ 2 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር አገኘች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቻይና ባለፉት 10 ወራት ለአሜሪካ ከላከቻቸው መኪኖች ሽያጭ 2 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር ማግኘቷ ተገለፀ፡፡

ቻይና ወደ አሜሪካ ከላከቻቸው የመኪና ወጭ ንግድ ከፍተኛ ገቢ ስታገኝ ከፈረንጆቹ 1992 ወዲህ ከፍተኛው መሆኑ ተገልጿል፡፡

ቻይና ወደ አሜሪካ ከላከቻቸው መካከልም÷ የጎልፍ እና ሀይብሪድ መኪኖች፣ የበረዶ ተሽከርከሪዎች፣ የአሌክትሪክ አውቶቡሶች እና ትራክተሮች እንደሚገኙበት ተጠቅሷል፡፡

ከላይ ከተገለጹት በበተጨማሪም አሜሪካ የመንገደኛ ተሽከርካሪዎችን ከቻይና እንደመታስገባ ፕራቫዳ የዜና ምንጭ ዘግቧል፡፡

ጃፓንን በመብለጥ ቻይና ከፍተኛ የመኪና አቅራቢ መሆኗን ያመላከተው ዘገባው÷ በ2023 ብቻ ከ5 ሚሊየን በላይ መኪኖችን በተለያዩ ሀገራት መሸጧን አስታውሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.